የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ባሌ ቅርንጫፍ ቀጥሎ የተጠቀሱትን የቁም ደኖች (ባህርዛፍ ግንድ ፤ ማገዶ እና አጠና) ለተለያዩ ኮንስትራክሽን ስራ የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የቁም ባህርዛፍ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር BOO3/OFWEBB/2017
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ባሌ ቅርንጫፍ ቀጥሎ የተጠቀሱትን የቁም ደኖች (ባህርዛፍ ግንድ ፤ ማገዶ እና አጠና) ለተለያዩ ኮንስትራክሽን ስራ የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
- በአሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ባሌ ቅርንጫፍ አሎሼ ባቱ ዲስትሪክት
በመሆኑም ተጫራቾች
- የግንዲላ ፤ የአጣና ፤ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች እንዲሁም ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ባሌ ጎባ መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሜድስን ፋካልቲ ፊት ለፊት በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ባሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመግዛት በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት እና የሚዘጋበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለፃል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ ( CPO ) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0226611679 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ባሌ ቅርንጫፍ
