የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምዕራብ ሪጅን ስር የሚገኙ ለደ/ዶሎ ፣ አሶሳ እና ለግልገል በለስ ቅ/ጽ/ቤቶች ቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት/ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ5 (አምስት ዓመት) ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምዕራብ ሪጅን
የቢሮ ኪራይ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምዕራብ ሪጅን ስር የሚገኙ ለደ/ዶሎ ፣ አሶሳ እና ለግልገል በለስ ቅ/ጽ/ቤቶች ቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት/ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ5 (አምስት ዓመት) ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ተወዳዳሪዎች:-
- የቤት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ /ፕላን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ኔትዎርክ ዝርጋታ ለማሰራት የቤቱ ባለቤት ፈቃደኛ የሆነ
- የሥራ ክፍሎች ብዛት የሚገልጽ በእስፔስፊኬሽን ውስጥ የተካተተ ይሆናል፡፡
- የቤቱ መገኛ ቦታ (Location) ቢያንስ ኮቦል መንገድ ዳር የሚገኝ፣
- የቤቱ/ህንፃው ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች ለመገልገል ሲመጡ የመግቢያ ደጁ አመቺ የሆነ አቀማመጥ ያለው
- ተጫራቶች ካሉበት ከተማ የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የተዘጋጀውን እስፔስፊኬሽን /ሰነድ/ ደ/ዶሎ ከተማ ያሉት ከደ/ዶሎ ቅ/ጽ/ቤት አሶሳ ከተማ ያሉት ከአሶሳ ቅ/ጽ/ቤት እና ግ/በለስ ከተማ ያሉት ከግ/በለስ ቅ/ጽ/ቤት በነፃ በመውሰድ ሞልቶው እስከ 15ኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ድረስ በፖስታ አሽገው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በነቀምቴ ከተማ በሚገኘው ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ሲለይ ተወዳዳሪዎች ውሉን በየቅ/ጽ/ቤቶች የሚዋዋሉ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ፦
➢ አሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 057-775-0249
➢ ደ/ዶሎ ቅ/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 057-555-0171
➢ ግ/በለስ ቅ/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 051-119-0439 ደውሎ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና
አስተዳደር ምዕራብ ሪጅን
