Tender Detail

Tender Details


የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ24/08/2017 ዓ.ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የግልጽና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ24/08/2017 ዓ.ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ል/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእታዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማለትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፤ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች ፡-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 24/08/2017 ዓ.ም እስከ 3፡45 ሰዓት እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ 5፡00 ሰዓት የኢታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ሰም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉብት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (አስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።

 

ተ.ቁ

የጨረታ ቦታ

የጨረታው ዓይነት

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

 

1

 

አዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

 

ግልጽ ጨረታና ሐራጅ ጨረታ

ጫማዎች፤ አልባሳት፤ ኮስሞቲክስ፤ የመኪና መለዋወጫ፤ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፤ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ የስፖርት እቃዎች፤ የእጅ ሰዓት፤ መነፅር፤ አሮጌ የመኪና ሞተሮች፤ ኮፐር መሳይ ብር፤ የወዳደቁ ብረት ብረቶች፤ ምግብ ነክ፤ ዘይትና ስኳር፤ ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

 

ለግልጽ ጨረታ በ24/08/2017 ዓ.ም እስከ 3፡45 ሰዓት፤ ለሐራጅ ጨረታ እስከ 4፡45 ሰዓት

 

ለግልጽ ጨረታ በ 24/8/2017 ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰዓት ለሐራጅ ጨረታ 5፡00 ሰዓት

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ቢታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  2. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል። አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርባቸዋል።
  3. ከላይ በተ.ቁ. 7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሰያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሸያጭ ይቀርባል።
  4. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

➢ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022-2-24-14-02 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፤

 

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender