መ/ቤታችን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጎዴ ቅ/ፅ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- ጎዴ/ግ/ጨ/001/2017
መ/ቤታችን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት መግለጫ |
የጨረታ ሠነዱ መግዣ ዋጋ (የማይመለስ) |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን በብር |
|
1 |
የቢሮ ኪራይ ጨረታ ለሶስት አመት የሚቆይ |
100.00 |
5,000.00 |
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጎዴ ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር በመምጣት 100 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ ታክስ ክሊራንስ ሰርተፊኬት / ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጎዴ ቅ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 5,000 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአገልግሎት ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ላይ ከተመለከተዉ የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል።
- ሠነዳቸውን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በአዲሱ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ስልክ 0962331133/0913562201/0913929850
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጎዴ ቅ/ፅ/ቤት
