የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የግዥ አፈፃፀም ስርአትን ለመወሰን ባወጣው መመሪያ ቁጥር 05/2011 መሠረት የተለያዩ እቅዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የግዥ አፈፃፀም ስርአትን ለመወሰን ባወጣው መመሪያ ቁጥር 05/2011 መሠረት የተለያዩ እቅዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት
- የጽህፈት መሳሪያ፤
- የጽዳት እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ፣
- ቋሚ እቃ፤
ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በጨረታ ለማስተላለፍ የሚያስችል ማስረጃ ወይም የአቅራቢነት የተሰጣቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው ::
ተጫራቾች ጨረታውን ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል የሰሜን ምስራቅ ሪጅን የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይቻላል።
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በሚገኘው ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በመሙላት በኮፒና በኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለጨረታ በታሸገ ሳጥን ውስጥ የሰሜን ምስራቅ ሪጅን የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 ማስገባት አለባቸው::
- ተጫራቾች ለተፈላጊ አቅርቦቶች የጠቅላላ ግዥውን ዓመታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በካሽ ጽ/ቤቱ በመቅረብ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው ::
- ጨረታው አየር ላይ በዋለበት በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈተውም በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት 8፡30 ሰዓት የሰሜን ምስራቅ ሪጅን የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 ነው። 16ኛው ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው ከላይ በተገለፀው ሰዓት በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል። አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 033 312 09 12
ሰሜን ምስራቅ ሪጅን የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
ደሴ
