በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት መደበኛ ካፒታል በጀት እና ካፒታል ፕሮጀክቶች ማለትም ለአስ/ር ህንጻ ግንባታ እና ለት/መንገድ ልማት ጽ/ቤት መንገድ ስራ እና በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የተለያዩ ማቴሪያሎዎችን በሀገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ሀገራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት መደበኛ ካፒታል በጀት እና ካፒታል ፕሮጀክቶች ማለትም ለአስ/ር ህንጻ ግንባታ እና ለት/መንገድ ልማት ጽ/ቤት መንገድ ስራ እና በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የተለያዩ ማቴሪያሎዎችን በሀገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡-
- ለወረዳው አስ/ር ጽ/ቤት ግንባታ የሚውል :- አሸዋ፤ ጠጠር፤ የፍልጥ ድንጋይ እና ብሎኬት ግዥ፤
- የህንጻ መሣሪያዎች እና የቧንቧ ዕቃዎች
- ዘመናዊ የንብ ቀፎ
- የደን ችግኝ ዘር እና የምግብ ምርጥ ዘር
- የመንገድ ከፈታ አፈር ሥራ የዶዘር ማሽነሪ ኪራይ/መኮናተር
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ተሻሽሎ በወጣው በመንግሥት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 28/2010 ዓ/ም መሰረት፡-
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር /Tin Number/ያላቸው፤
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትን መረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከሽያጭ ዋጋ ላይ ለመንግሥት ግብር 2% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ፤
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የዕቃ አቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጨረታ ሁኔታ በአይተም ወይም በጥቅል ሊሆን ይችላል፤
- የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለዶዘር ማሸን ከመንግሥት መ/ቤት የመልካም የስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቹ የግል ሊብሬ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፤
- የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በመለየት ኦርጂናሉን በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በሰም በታሸገው ኤንቨሎፕ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በቁጫ አልፋ ወረዳ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ-5 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ሂደቱ ላይ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 10% የማስያዝ ግዴታ አለበት፤
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ወደ ቀጫ አልፋ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-5 ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በጥሬ ወይም የኢትዮ ባንክ ቼክ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ህጋዊ CPO ለሚሳተፉበት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ የሚታሸገው የጨረታ ማብቂያ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10:00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃውን እስከ ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ የጫኚ አውራጅና የጭነት ወጪን በመሸፈን ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች ወይም የጨረታ ወኪል ያለመገኘት ጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡
- 16ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- የደን ችግኝ ዘር እና የምግብ ምርጥ ዘር ግዥ ጨረታ ተወዳዳሪዎች ከቫት ነጻ የሆኑበትን የድጋፍ ደብዳቤ መረጃ አያይዞ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ለዶዘር ማሽነሪ ኪራይ ሞዴል ከ2010 ወዲህ ስሪት CAT D8R በአሁኑ ገበያ ያለ መሆን አለበት፡፡
- ለዶዘር ማሽን የጭነት ዋጋ በአከራዩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- የዶዘር ማሽን አሸናፊ ተጫራች በውድድሩ ካሸነፉ በሰባት ቀናት ውስጥ ለአሰሪው መ/ቤት ማሽኑን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃው ከጥራትና ደረጃ ዝቅ ቢል፣ ዕቃው ቢጎድል ከተዋወለው ከውሉ ጊዜው ቢያልፍ በሕግ መሰረት ለመንግስት ከገባው ከጠቅላላ ውል ገንዘብ ላይ 20% የሚደርሰውን ብር ተቀጥቶ ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ በፍ/ህ/ቁጥር 2005 መሰረት የፀና ይሆናል ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መበቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ፡- 0916669982/0926366087/0976135648/ 0984666189 ደውለው ይጠይቁ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የቁጫ አልፋ ወ/ፋ/ጽ/ቤት
