የአንድነት ፓርክ የመኪና መቆያ ህንፃ (ፓላስ ፓርኪንግ) ለቢሮ/ለሱቅ የሚሆኑ ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።
Unity Park Ethiopia (አንድነት ፓርክ ኮርፖሬሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 2/2017 ዓ.ም
የአንድነት ፓርክ የመኪና መቆያ ህንፃ (ፓላስ ፓርኪንግ) ለቢሮ/ለሱቅ የሚሆኑ ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰነድ ቅደም ተከተል መሰረት ቫትን ጨምሮ ነው።
- ተጫራቾች የቦታውን ግምት በካሬ በተቀመጠው የመነሻ ዋጋን ተንተርሶ የሚያቀርቡ ይሆናል። የሚያሸንፉበት ቦታ ላይ ለሽያጭ የሚያቀርቡትን እቃ እና አገልግሎት ዋጋ እንዲሁም የድርጅታቸውን ሙሉ ፕሮፋይል ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 305 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የቦታውን ጠቅላላ ሁኔታ በስፍራው በመምጣት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በስራ ሰዓት መመልከት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን 8፡15 ላይ ይከፈታል።
- እያንዳንዱ ተጫራች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በጽ/ቤቱ ስም ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ከተሰማሩበት ንግድ ስራ ዘርፍ ውጭ በሆነ የንግድ ፈቃድ መወዳደር አይችልም።
- ፓርኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- +25 11 140 0750/ +251 11 857 8718
አንድነት ፓርክ ኮርፖሬሽን
