Tender Detail

Tender Details


የኦሮሚያ ግብርና ኅ/ሥ/ማ ፌዴሬሽን ኃ/የተ/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ከህጋዊ ንግድ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኦሮሚያ ግብርና ኅ/ሥ/ማ ፌዴሬሽን ኃ/የተ/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ከህጋዊ ንግድ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት-1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች፤ ሎት 2 የጽዳት እቃ፤ ሎት-3 የደንብ ልብስ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፣

  1. ተጫራቾች በዚህ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ ፤ቫት ሰርተፊኬት ፤ ቲን ቁጥር ሰርተፊኬት የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡
  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል ጨረታ ሰነዱን ከኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን አዲስ አበባ ጀርመን አደባባይ ወደ ጀሞ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACF ህንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 በመገኘት ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተከታታይ ቀናት ብቻ መውሰድ ይችላሉ ፡፡
  3. ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት በ16ኛው ቀን ሲሆን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ በማስያዝ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
  6. ተጨማሪ ማብራሪያ ከድርጅቱ መረዳት ይቻላል፡፡

አድረሻ፡- አዲስ አበባ ጀርመን አደባባይ ወደ ጀሞ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACF ህንፃ 6ኛ ፎቅ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12

ስልክ:- 09-04-61-37-32

የኦሮሚያ ግብርና ኅ/ሥ/ማ ፌዴሬሽን ኃ/የተ/

 

Save Tender