በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Abbay Basin Administration Office (አባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት)
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ቁጥር ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ.ቤ.አስ.ጽ/01.2/2017
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የጨረታው ሰነድ የሎት (lot) መለያ
- ሎት - 1. የላቦራቶሪ እቃዎች እና ኬሚካል
- ሎት - 2 የደንብ ልብስ
- ሎት -3 ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት -4 የመኪና ጎማ
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለተፈለገ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በዘርፋ የተሰማሩ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቡድን 1ኛ ፎቅ. ቢሮ ቁጥር 119 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት
- ሎት- 01 የላብራቶሪ ኬሚካል ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- ሎት- 02 ደንብ ልብስ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት 03 ኤሌክትሮኒክስ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 04 የመኪና ጎማና ባትሪ ብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር)
በአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ እና በድርጅቱ ማህተም በተደረገበት ፖስታ እያንዳንዱ ፖስታው ላይ ተጽፎ ባህር ዳር ብልጽግና ጽ/ቤት ጎን ከሚገኘው የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 15 ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች ወይም ተወካዮች አለመገኘት የጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ወይም ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከጽ/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583216896 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት
