የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል በኤሌክትሪክ የሚሠራ ሞተር ሣይክል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Sidama National Regional State Road Development &Transport Bureau (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 05
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውል በኤሌክትሪክ የሚሠራ ሞተር ሣይክል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት ዕቃዎች በውድድር መስፈርት መሠረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የአቅርቦት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይመለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00-6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀውየጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) በCPO ወይም ህጋዊ ባንክ ጋራንቲ (Unconditional Bank Guarantee) ለ90 ቀን ፀንቶ የሚቆይ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ በሁለት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ላይ ብቻ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ በቴክኒካል ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ለ3 ወራት (90 ቀናት) ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) ከፍለው ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 104 በአካል ቀርበው መግዛት ይቻላል፡፡
- በኤሌክትሪክ የሚሠራ ሞተር ሣይክል ጠቅላላ ዋጋ ድምር ላይ የተሰራው የድምር ስህተት 2% በመብለጥም ሆነ በማነስ ከሆነ ከጨረታ ውድድር ውድቅ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በመ/ቤቱ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ ብቻ የአንድ ነጠላ ዋጋን ዕቃውን ብዛት በማስላት በትክክል አጠቃላይ ድምር ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0462121455/0462122050
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ሀዋሳ
