በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa Driver and Vehicle Licensing and Control Authority (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- አሽተሽፍቁባ/መግዳ/2017/003
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ሎት 1. የመንጃ ፍቃድ ካርድ ፕሪንተር፣ ሪቫን፣ ላምኔሽንና መንጃ ፈቃድ ካርድ
- ንግድ ምዝገባ፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (ቲን ነምበር)፤ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፊኬት ለእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከእሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና መስሪያ ቤት መክሊት ሕንፃ 8ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 804 ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ገዝታችሁ መውሰድ ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት ለእያንዳንዱ ሎት በተናጠል (ለየብቻ) በባንክ የተረጋገጠ CPO አሠርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ለሎት 1 የ500,000 ብር (አምስት መቶ ሺህ ብር) CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ባለሥልጣን መሥሪያቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ውይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡- ከጐላጐል ታወር ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ መክሊት ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር (708)፤
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-6-67-23-36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን
