Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Health Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ የአውሮፕላን ማረፊያ መንገድ ከሆምላንድ ሆቴል ፊት ለፊት ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-222-1127
  • Websitehttps://www.arhb.gov.et/
  • Deadline22 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-22 00:00:00
  • Categories Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጤና ቢሮ ከመደበኛ በተገኘ የበጀት ድጋፍ በክልሉ ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት እና ለቢሮው አገልግሎት የሚውል የህክምና መገልገያ መሳሪያ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል::

Amhara Health Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጤና ቢሮ ከመደበኛ በተገኘ የበጀት ድጋፍ በክልሉ ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት እና ለቢሮው አገልግሎት የሚውል የህክምና መገልገያ መሳሪያ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ፣
  3. ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡።
  4. የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት::
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ::
  6. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በታሽገ ፖስታ በጤና ጥበቃ ቢሮ በግዥ /ፋይ/ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል /ቢሮ ፋይናንስ ህንፃ በ16ኛው ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
  8. ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት እና በአስራ ስድስተኛው ቀን እስከ 8፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ በብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል ቀርቦ መግዛት ይችላል::
  11. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጭ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት::
  12. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  13. ተጫራቾች በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ ጨረታውን ላወጣ መስሪያ ቤት ለአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ፋይናንስ ህንፃ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-2-22-11-27 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል::

 

የአብክመ ጤና ቢሮ

 

Save Tender