የሀዋሳ ከተማ መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት የጽህፈት መሳሪያ እና የፅዳት መገልገያ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ ውሃ ማዕድንና እና ኢነርጂ ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች እና የፅዳት መገልገያ ዕቃዎች
የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጽህ/10/2017
የሀዋሳ ከተማ መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት የጽህፈት መሳሪያ እና የፅዳት መገልገያ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተገለፀው ዝርዝር መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
|
ሎት |
መግለጫ |
መለኪያ |
|
1 |
ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች |
ቁጥር |
|
2 |
ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የፅዳት መገልገያ ዕቃዎች |
ቁጥር |
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የ2017 ዓ.ም የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ድፈቃድ ያለው እና የተጨማሪ እሴትታክስ ( የቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣
2. የጨረታ ዋስትና መያዣ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ግዥውን በሚፈፅመው ድርጅት ሥም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ እንድሁም ከተጠየቀው ሲፒኦ ማስያዣ ውጪ የቀረበ ጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
3. የተዘጋጀውን የዕቃ ዓይነት ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 500.00 / አምስት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ከሀዋሳ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 19 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንቱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ ይዞ መምጣት አለበት፡፡ ሠነድ ካልያዙ የጨረታ ዶክመንቱ አይሸጥም።
5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና 2 (ሁለት) ኮፒ ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት ከጠዋት 2፡30 ሰዓት እስከ 11.00 ሰዓት ድረስ ከሀዋሳ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 19 በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች በ21ኛው ቀን የጨረታ ዶክመንቱን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በ21ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸ በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም 21ኛው ቀን የስራ ቀ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
10. በጨረታ መከፈቻ ዕለት ለሁሉም ዕቃዎች ከአንድ በላይ አማራጭ ሳምፕል ይዞ መቅረብ አለበት፡፡ በዕለቱ ሳንፕሉን ይዞ ያልተገኘ ተጫራች የጨረታ ዶከመንቱ ሳይከፈት ተመላሽ ይደረግለታል።
ስልክ ቁጥር- 046 212 1580/ 046 22129112
አድራሻ :- ከወልደአማኑኤል አደባባይ በግራ በኩል ወደ አዲሱ መናኸሪያ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር አስፋልት
በሲዳማ/ብ/ክ/መንግስት የሀዋሳ ከተማ ውሃ እና/ፍ/አገ/ድርጅት
