አበበች ጎበና ቻሪቲ የተለያዩ አዲስና ያገለገሉ አልባሳትና ቁሳቁሶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Abebech Gobena Charity (አበበች ጎበና ቻሪቲ)
የጨረታ ማስታወቂያ
አበበች ጎበና ቻሪቲ የተለያዩ አዲስና ያገለገሉ አልባሳትና ቁሳቁሶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ማንኛውም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የሚወዳደርበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በማስገባት መወዳደር ይችላል።
ጨረታው ሚያዝያ 16 ቀን 2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፦
-
ከላይ በተገለፁት 10 የስራ ቀናት ውስጥ እቃዎቹን በቦታው ተገኝቶ ማየትና የጨረታ ሰነዱን ከአስተዳደር ቢሮ የማይመለስ ብር 1000 ከፍሎ መግዛት ይቻላል።
-
ተጫራች ካቀረበው የመወዳደሪያ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ በካሽ ወይም በባንክ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
-
ለጨረታ ማስከበሪያ የከፈሉበት ደረሰኝ ሲፒኦ እና የንግድ ፈቃድ ኮፒ ከመወዳደሪያ ሰነዱ ጋር መያያዝ ይኖርበታል።
-
ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
አድራሻ፡-
አበበች ጎበና ቻሪቲ አዲስ አበባ ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፣ አባኮራን ሰፈር
ስልክ፡- 0948-777776
አበበች ጎበና ቻሪቲ
