የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በአስኮ በላምበረት አየር ጤናና ቃሊቲ የሚገኙ መናኸሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ቢሮዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
Ministry of Transport and Logistics (የትራንስፖርት እና ሎጁስቲክስ ሚኒስቴር)
የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 01/2017
ለቢሮ እና ለንግድ አገልግሎት የሚውል የቢሮ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በአስኮ በላምበረት አየር ጤናና ቃሊቲ የሚገኙ መናኸሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ቢሮዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
-
ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ማስረጃ/ታክስ ክሊራንስ / ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመስሪያ ቤቱ አካውንት ቁጥር 1000000984365 በማስገባት ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ በጨረታ ሰነዱ ላይ እስከተገለጸበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የግዥ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 204 መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /Bid bond/ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /cpo/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ከባንክ የሚቀርበው ዋስትና ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
-
ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 204 ግዥ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ ለዚህ ብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
-
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በጨረታ ሰነዱ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ፡- እስቴዲየም አካባቢ / ቤተዛታ ጎን
ለተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ በስልክ ቁጥር ፡- 0115588958 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
የትራንስፖርት እና ሎጁስቲክስ ሚኒስቴር
