የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የወረታ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጥበቃ እና ጽዳት አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ወረታ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
RFQ: ESLSE/P&T/NEG/2025/01859 2017
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የወረታ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጥበቃ እና ጽዳት አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መጫረት የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
-
በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያሳይ መረጃ (Tax Clearance)፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ ከ500,000.00 ያልበለጠ በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ “የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት” በሚል ስም በማሰራት ከጨረታ ፖስታው ጋር በማቅረብ መጫረት ይችላሉ፡፡
-
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ የሚመልሰው በድርጅቱ ድረ ገጽ (www.eslse.com) (በERP System Link:-https://ehog.fa.em2.oraclecloud.com/fscmUI/faces/PrcPosRegisterSupplier?prcBuld-300000003585149 በዋና መ/ቤት ምዝገባ ካካሄዱ በኋላ ብቻ (ከዚህ ቀደም ያልተመዘገቡ ከሆነ) በሚሰጣቸው መለያ ቁጥር መሠረት የሚሞሉ መሆኑን እናሳውቃለን::
-
የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ቀን እና ሰዓት ይሆናል፡፡
-
ሲስተሙ ጨረታውን ከዘጋ በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
-
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ወረታ ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት
ደቡብ ጎንደር (ወረታ)
