በማዕከላዊ ኢትዮ/ክ/በስልጤ የዳሎቻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017ዓ.ም ለጤና ተቋማት ለሕክምና አገልግሎት የሚውል የአልትራሳውንድ ማሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የዳልቻ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮ/ክ/በስልጤ የዳሎቻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017ዓ.ም ለጤና ተቋማት ለሕክምና አገልግሎት የሚውል የአልትራሳውንድ ማሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
-
የዘመኑን ግብር አጠናቆ የከፈለ ስለመሆኑ ማስረጃ የሚያቀርብ
-
በመስኩ የንግድ ፈቃድ ያለው
-
የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
-
የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ
-
በህከምና መገልገያ ሽያጭ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የሚያቀርብ
-
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ ወይንም እውቅና ካለው ተቋም የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ ቢድ ቦንድ ማስያዝ የሚችል፡፡
-
በዘርፉ መወዳደር የሚፈልግ ሰነዱን ከስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር8 በመቅረብ ለሰነዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የሚችል መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በስልጤ ዞን በዳሎቻ/ወ/ፋይናንስ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8:30 መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፦
-
ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡
-
የተወዳዳሪ ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጥም፡፡
-
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ 0464660141/142/0949018751 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የዳልቻ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
