በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር በምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክት ማህበራትና ድርጅቱ በጋራ የሚያስተዳድሩት የቁም ባህር ዛፍ ደን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
OFWE/BA-04/2017
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር በምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክት ማህበራትና ድርጅቱ በጋራ የሚያስተዳድሩት የቁም ባህር ዛፍ ደን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
- የጊንድላ፣ የአጣና የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል /አይልሊቢያ/ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ወይም ጨረታው የወጣበት ፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋጀው ; የሚታሸገው እና የሚከፈተው በሞጆ ከተማ በምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክት ቅ/ጽ/ቤት ነው::
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (cpo) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 0111240249 መደወል ይችላሉ
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
