የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንብረት የሆኑትን ተሽከርካሪዎችን) መኪናዎችን ለማስጠገን የጥገና ጋራዥ አገልግሎት ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንብረት የሆኑትን ተሽከርካሪዎችን) መኪናዎችን ለማስጠገን የጥገና ጋራዥ አገልግሎት ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟስ ድረጅቶች መወዳደር ይችላሉ።
- በሥራ ዘርፉ ተደራጅተው ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- ጋራዡ ሙሉ የኢንሹራንስ ሽፋን ያለውና የ2017 ዓ.ም የታደሰ መሆን አለበት፡፡
- ከክልሉ የመንገድ ትራንስፖርት የብቃት ማረጋገጫ ያቀረበ መሆን አለበት፤
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ተኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ስራውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ሳምፕል ይዛቹ እንድትቀርቡ፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 046-2-12-13-31
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
