የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል የመኪና ጥገና አገልግሎት ጨረታ
የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 06/19
በሲዳማ ብ/ክ/መ/ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ህጋዊ ዕውቅና ካላቸው ድርጅቶች ከታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- መኪና ጥገና
በመሆኑም በንግድ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ ስፔሲፊኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከማዕከሉ ግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና CPO ቴክኒካል ዶክሜንት ውስጥ በማድረግ አጠቃላዩን በአንድ ፖስታ በማሸግ በማዕከሉ ግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ የግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ይከፈታል። ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመክፈቱ ሥነ-ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል።
- ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጊዜ ወይም በቦታው ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም።
ማዕከሉ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር፡- 0462129501/ 0462129504 ይደውሉ።
የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል
✨ messages.ai_summary
Hawassa Cattle Semen Production, Processing and Distribution Center (Sidama Livestock Resources Development Bureau) seeks a garage service provider for vehicle maintenance. Open to licensed providers with TIN and supplier registration. Open bid.
