Tender Detail

Tender Details

  • Company ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address 22 ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251118212214
  • Website
  • Deadline07 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-07 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በጨረታ መለያ ቁጥር አአከአአድ/መጋሱኪ/ብግጨቁ001/2017 በአዲስ አበባ መርካቶ የአውቶቡሶች ተርሚናል የሚገኙትን መጋዘኖች እና የንግድ ሱቆችን ኪራይ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)


 

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በጨረታ መለያ ቁጥር አአከአአድ/መጋሱኪ/ብግጨቁ001/2017 በአዲስ አበባ መርካቶ የአውቶቡሶች ተርሚናል የሚገኙትን መጋዘኖች እና የንግድ ሱቆችን ኪራይ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-

1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade licensee)፣

2. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፡

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)፣

4. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፣

5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በተወዳዳሪው የቀረበውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በማቅረብ በግልጽ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ሆኖ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር8-01 መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦሪጅናል ዶክመንት በአንድ ኤንቨሎፕ እና ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኮፒ ዶከመንት በአንድ ኤንቨሎፕ በማሸግ በፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 8-01 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ 15 ቀናት ሆኖ በ15ኛው ቀን እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ በ15ኛው ቀን ጨረታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 8-01 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታው መክፈቻ ቀን የበዓላት ቀን የሚውል ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስልክ ቁጥር፡ 0116-66-33-67

 

የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender