Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0462121127
  • Website
  • Deadline06 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-06 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ


 

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-

1. ሎት 1-የሞተር ሳይክል ግዥ

2. ሎት 2- የመጋረጃ ግዥ

  • በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
  • የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴክኒካል ኦሪጅናል 1 እና 2 ፎቶ ኮፒ ፋይናንሻል ኦሪጅናል 1 እና 2 ፎቶ ኮፒ በA4 ወረቀት ለአንድ ወረቀት አንድ ኮፒ ብቻ በማድረግና በማዘጋጀት እያንዳንዱን በተናጠል በፖስታ በማሸግ በፖስታው ውጭ የሰነዱን ዓይነት ኦሪጅናል ወይም ኮፒ መሆኑን በመፃፍ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር )ብቻ CPO ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጉዳይ የተዘጋጀ የዕቃዎቹን ዝርዝር መግለጫዎችን የያዘ ሰነድ / Specification / ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 005 በ50 (ሀምሳ ብር) ብቻ በመግዛት ሰነዱ ላይ በመፈረም እና የድርጅታቸውን ማህተም በማሣረፍ ለዕቃዎቹ የሚያቀርቡትን ዋጋ በድርጅቱ በዋጋ መሙያ ፎርም ላይ በመሙላት ቫትን ያካተተና ያላካተተ ስለመሆኑ በመግለፅ ፖስታውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ16ኛው ቀን እስከ 6፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 005 ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን እንዲያስገቡ እያሳሰብን ጨረታው 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል።

 

ማሳሰቢያ፦ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ.ቁ 0462121127/0462121126

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ

Save Tender