በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ለ2017 የበጀት ዓመት ለሚያስተምራቸው ተማሪዎች የምግብ አቅርቦት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Kombolcha College of Agriculture (ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ለ2017 የበጀት ዓመት ለሚያስተምራቸው ተማሪዎች የምግብ አቅርቦት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ማለትም፡- ሎት1 የተለያዩ አትክልቶች (ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭሽንኩርት፣ ቃሪያ) ሎት2 የባልትና ውጤቶችን (አተር ክክ፣ ምጥን ሽሮ እና በቂ ቅመም ያለው የተዘጋጀ በርበሬ)፣ ሎት3 ዳቦ ፣ሎት4 ሸቀጣሸቀጥ (ቲማቲም ድልህ 850 ግራም /ሣልሳ/፣ 1ኛ ደረጃ ሩዝ፣ ፖስታ ባለ 500 ግራም ፤ የምግብ ጨው ሻይ ቅጠል ባለ100 ግራም) እና ሎት5 የተፈጨ የበሬ ስጋ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለማቅረብ አግባብ የሆነና በየዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ በደንብ በሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር በተናጠል A4 ወረቀት በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፀውንና በየዘርፉ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 10 መግዛት ይቻላል፡፡
- ከአንድ ዘርፍ በላይ ለምትሳተፉ ተጫራቾች ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የጨረታውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት CPO ቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡ ከዚህ ውጭ ያቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 2/7/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 12 ዘወትር በስራ ሰዓት በጥሩ ሁኔታ በታሸገ ፖስታ ኮፒ እና ኦሪጅናል በማለት የድርጅታቸውን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታውም በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0335510186 /0335514206/07 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ
