በአራዳ ክ/ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ ፣ የህትመት ስራዎች እና የህክምና መገልገያ መሳሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ የአዋሬ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክ/ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ ፣ የህትመት ስራዎች እና የህክምና መገልገያ መሳሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
1) ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2) በመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው፡፡
3) ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4) ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ከአራዳ ክ/ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ላይ የግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 403 ቀርበው 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው ሰነዱን በመውሰድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን የእንዱን ዋጋ ቫትን ያካተተ በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
10) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የሚጫረቱበት ዋጋ ለፅህፈት መሳሪያዎች /አላቂ የቢሮ ዕቃዎች/፤ ለፅዳት እቃዎች የደንብ ልብስ ፣ለህትመት ስራዎች ለእያንዳንዱ /2.000.00/ ሁለት ሺህ ብር ብቻ/ እና የህክምና መገልገያ መሳሪዎች /8,000.00/ ስምንት ሺህ ብር/ብቻ/ ለአራዳ ክፍለ ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ ስም ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ /C.P.O/ በታሸገ ኤንሸሎፕ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5) ተጫራቾች ለጨረታው የገዙበትን ኦሪጅናል ሰነድና ኮፒውን በሁለት ፖስታ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
6) ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ እና የጽዳት እቃዎች የአገልግሎት ዘመናቸው አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው::
7) ተጫራቾች ከገዙበት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
8) የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በአስራ አንደኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 408 በግልጽ ይከፈታል፡፡
10. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው።
♦ አድራሻ፡- በቀድሞ ስሙ የካ ክ/ከተማ አቧሬ ጤና ጣቢያ ተብሎ የሚጠራው በአሁኑ በአራዳ ክ/ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ ንጋት ኮከብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 404
♦ ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር 0118688278 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ የአዋሬ ጤና ጣቢያ
