Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ)
  • Address ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ኤም. ኤ ህንፃ 13ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118125085
  • Websitehttps://addiscadaster.gov.et/
  • Deadline28 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የ2017 በጀት ዓመት የቢሮ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር LHRIA/NCD/003/2017 ዓ.ም

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የ2017 በጀት ዓመት የቢሮ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሚገዛው ዕቃና ተዛማጅ አገልግሎት ግዥ

ሎት 1 - የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሣሪያዎች ግዥ

ሎት 2 - ኮምፒውተር፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች

ሎት 3 - የፎቶ ኮፒና ፕሪንተር ቀለሞች

ሎት 4 - የመኪና ጎማና ጌጣጌጥ እቃዎች

ሎት 5 ፡- ሌሎች የቢሮ መገልገያ እቃዎች በመሆኑም በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. ተጫራች ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1. 3000 ብር /ሶስት ሺህ ብር/፣ ለሎት 2. 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ ለሎት 3. 10,000 ብር /አስር ሺህ ብር/፣ ለሎት 4. 4500 /አራት ሺህ አምስት መቶ ብር/፣ ለሎት 5. 5500 /አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር/፣ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ኤጀንሲው እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ፋይናንስ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም ቴክኒክ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ትክክለኛውን ቅጅ በእያንዳንዱ ሎት ለየብቻው በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቁት እቃዎች ከጨረታው መክፈቻ ቀደም አድርገው ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከተጠቀሰው ቀን ዘግይቶ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት አይኖረውም።
  7. የጨረታው ፋይናንስ ሰነድ የሚከፈተው እና ግምገማ የሚካሄደው ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተመለከቱት ቴክኒካል መረጃዎች እና የእቃው ናሙናዎች በትከክል ተሞልቶ መቅረባቸው ሲረጋገጥ ነው፡፡
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 እና ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ኤም. ኤ ህንፃ 13ኛ ፎቅ የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት በመምጣት የማይመለስ 300 ብር/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች ዋጋ መሙላት ያለባቸው ኤጀንሲው በክፍል 4 ባቀረበው የዋጋ መሙያ ብቻ ሲሆን በራሳቸው የዋጋ መሙያ ያቀረቡ የንግድ ድርጅቶች ከጨረታ ውድድር ይሰረዛሉ፡፡
  11. ኤጀንሲው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይቻልም፡፡
  13. ኤጀንሲው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡- ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ኤም. ኤ ህንፃ 13ኛ ፎቅ የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ወይም በስልክ ቁጥር 0118125085 ደውለው ያነጋግሩ፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

 

Save Tender