በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ የመለያ ቁጥር 02/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ሎት 1. ደንብ ልብስ 20,000 ብር ( ሃያ ሺህ ብር)
ሎት 5. የፅዳት እቃዎች — 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)
ሎት 2. የጽሕፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ——— 30,000 ብር (ሰላሳ ሺህ ብር)
ሎት 3. ህትመት -10,000 (አስር ሺህ ብር)
ሎት 4. መድኃኒትና የላብራቶሪ ዕቃዎች -100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
ሎት 5. የፅዳት እቃዎች- 10,000 (አስር ሺህ ብር)
ሎት 6. ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች --- 50,000 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር)
ሎት 7. የእንጨትና የብረት ውጤቶች—– 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)
ሎት 8. የጥገና ሥራዎች —20,000 (ሃያ ሺህ ብር)
ከተለያዩ ህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፤
1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣
2. የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
3. የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
4. በዘርፉ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣
5. ቲን Tin No (ቁጥር) ያላቸው፤
- የጨረታ ዋጋ የሚሞላው ከጤና ጣቢያው በገዙት ሰነድ ላይ ሲሆን የሚወዳደሩበትን ዘርፍ ሁሉንም መረጃዎች በሚገባ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም። አስቸጋሪ ሁኔታ ካገጠመ የቀድሞው ቁጥር ሊነበብ በሚችልበት ሁኔታ በአንድ መስመር ብቻ ይሰርዙት፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የአቅርቦት ዘርፍ ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ እንዲሁም የግርጌ ድምር በመደመር የጠቅላላውን ዋጋ ማሳየት አለባቸው:: የሚሞሉት የነጠላና ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን /VAT/ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያቀርቡት ለቋሚ ዕቃ ለሚሰጠው አገልግሎት ቢያንስ የአንድ ዓመት ዋስትና ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናሉንና የሌሎች ማስረጃዎችን ለብቻው በአንድ ፖስታ፣ ሲፒኦ ደረሰኝ በአንድ ፖስታ፤ እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን ኮፒ በአንድ ፖስታ በማድረግ በሚገባ በማሸግ በጀርባቸው ላይ ኦሪጅናል፤ ኮፒ፤ እንዲሁም ሲፒኦ በሚል መጻፍና እንደገና ሁሉንም ለብቻቸው የታሸጉ ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሚገባ በማሸግ በፖስታው ጀርባ ላይ ኦሪጅናል፤ ኮፒ ሲፒኦ በሚል መግለጽ አለባቸው::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ በሞሉበት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ እና በየደረጃው በታሸጉት ፖስታዎች ላይ የድርጅቱን የበላይ ኃላፊ ፊርማና ሥም እንዲሁም ህጋዊ ክብ ማህተም ማሳረፍ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 በተዘረዘረው መሰረት የሞሉትንና ያዘጋጁትን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት በመንግሥት የሥራ ሰዓት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀውና በጤና ጣቢያው የግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 414 በተቀመጠው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- በተጫራቾች የተሞላው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሂደት የማጭበርበር (የሙስና) ተግበር ሲፈጽሙ ቢገኙ ወይም ለመፈጸም ቢሞክሩ በኢትዮጵያ ሕጎች የተደነገገው ተፈጸሚ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሂደት ለማዛባት ቢሞክሩ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ከጨረታው ይሰረዛሉ፤ በቀጣይም በመንግሥት ግዥዎች እንዳይሳተፋ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የእያንዳንዱን እቃ የሚመለስ ናሙና ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ለጤና ጣቢያው ባዘጋጀው ክፍል በአደራ ማስረከብ አለባቸው፡፡ ናሙና ለማቅረብ የሚያስቸግሩ እቃዎችን ፎቶ ግራፊና ዝርዝር መግለጫቸውን በማያያዝ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ማሳሰቢያ፡- ናሙና ሲያመጡ (ሲያቀርቡ) የድርጀቱ ማህተም መደረገ የለበትም፤ ነገርግን ምልክት አድርጎ ያቀረበ አቅራቢ የመጣው ናሙና ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ተጫራች ውል እስኪገባ ድረስ ተመላሽ አይሆንም።
- የጨረታ ሳጥንኑ በ11ኛ (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ለይ የሚዘጋ ሲሆን የተጠቀሰው ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም::
- ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ በጤና ጣቢያው አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩት በመጀመሪያ በዕቃ ጥራት ሲሆን በሁለተኛው ደረጃ የሚያቀርቡት ዝቅተኛ የዋጋ መጠን ሆኖ ሁለት ተጫረቾች እኩል ነጥብ ቢያመጡ የግዥ መመሪያና ደንቡ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 % (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/C.P.O /ሲፒዮ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ውል ሲፈፀምም ሆነ ከተፈጸመ በኋላ በጨረታው ሰነዱ ላይ ከሞሉት ዋጋ ውጭ ምንም አይነት ማስተካከያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቶች ከፍያ የሚፈፀምላቸው እንዲያቀርቡ የታዘዙትን ዕቃ በታዘዙበት ጊዜ በራሳቸው ወጪ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል በማቅረብ ሙሉ በሙሉ ሲያስረክቡና የንብረት ገቢ ደረሰኝ ሲያቀርቡ ነው።
- በግዥ አፈጻጸሙ ላይ በደል ደርሶብኛል የሚል ተጫራች ለአቤቱታው መሰረት የሆነውን የመጫረሻ ውሳኔ ከሳወቀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5 /አምስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ጨረታ ላወጣው የመንግሥት መ/ቤት የበላይ ኃላፊ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የበላይ ኃላፊው መልስ ካልሰጠ ወይም በሚሰጠው መልስ ያልረካ ቅሬታ አቅራቢ ውሳኔው መስጠት ከነበረበት ጊዜ ገደብ ማብቂያ ጀምሮ በሚቆጠር 5 /አምስት/ የሥራ ቀን ጊዜ ውስጥ አቤቱታውን ለአጣሪ ኮሚቴ ማቅረብ ይችላል፡፡ ከዚህ ግዜ በኋላ ለአጣሪ ኮሚቴው የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ከተጫራቹ ጋር ከገባው የግዥ ውል አቅርቦት መጠን ላይ በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀር እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-68-61-09-20 ወይም ቢሮ ቁጥር 414 በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አሸናፊ ወይም አቅራቢ ድርጅት የአሸነፈበትን እቃ ገቢ ለማድረግ ደረሰኝ ሲያቀርብ የካሽ ሪጅስተር ከአታችመንት ጋር (የእጅ በእጅ ደረሰኝ) ከሆነ ከገቢዎች ደረሰኝ እንዲጠቀሙ የተፈቀደበት ደብዳቤ ማጻፍ አለባቸው፤ ይህ ካልሆነ ግን እቃውን ገቢ ማድረግ የማይቻል መሆኑን በትህትና እናሳውቃለን፡፡
- ከጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ አቅራቢዎች የድጋፍ ደብዳቤ አጽፈው መምጣት ያለባቸው ከአደራጃቸው የጽ/ቤት የበላይ ኃላፊ ተፈርሞ መቅረብ አለባቸው፡፡ ነገርግን በቡድን መሪ ተፈርሞ የሚመጣ የድጋፍ ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም፡፡
ማሳሰቢያ :-
* በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አቅራቢዎች የሚወዳደሩት በሚያመርቱት ምርት (ዕቃ) ብቻ መሆኑን አውቀው የአምራች (አቅራቢ) የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ይህ ካልሆነ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
ነገር ግን በማያመርቱት ምርት (ዕቃ) መወዳደር የሚችሉት እንደማንኛውም ተጫራች ሲፒኦ ማቅርብ (ማስያዝ) አለባቸው፡፡
* የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ግዜ 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በመንግስት በስራ ሰዓት ጤና ጣቢያ አራተኛ ፎቅ ረዳት ፋይናንስ ክፍል ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ጥብቅ ማሳሳቢያ :-
* መድኃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት የሚወዳደሩ አቅራቢዎች፡- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው::
በጥገና ሥራዎች ላይ የሚወዳደሩት አቅራቢዎች፡-
የጀኔነተር ጥገናዎች በዘርፉ የስራ ልምድና ተያያዥ ደጋፊ ዶክመንት ያለው በቅድሚያ ይታያል
የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንክ በተረጋገጠ CPO (ሲፒኦ) ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
የጨረታ ማስከበሪያ ለምሳሌ ቢድ ቦንድና የባንክ ጋራኒቲ ቢቀርብ በምንም ተቀባይነት እንደማይኖረው በትህትና እናሳውቃለን፡፡
አድራሻ ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰሚት ጤና ጣቢያ
