የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት በኢንስቲትዩቱ ግቢ ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ለባንክ፣ ለቢሮ (ትኬት መሸጫ ቢሮ) : ለሚኒ ሱፐርማርኬት ፡ ለካፌ( ለሻይ ቡና ኬክ ለመሳሰሉት) የሚውሉ የተለያየ ስፋት ያላቸውን ክፍሎች ማከራየት ይፈልጋል፡፡
Institute of Ethiopian Standards (የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት)
በድጋሚ የወጣ የህንጻ ኪራይ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት በኢንስቲትዩቱ ግቢ ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ለባንክ፣ ለቢሮ (ትኬት መሸጫ ቢሮ) : ለሚኒ ሱፐርማርኬት ፡ ለካፌ( ለሻይ ቡና ኬክ ለመሳሰሉት) የሚውሉ የተለያየ ስፋት ያላቸውን ክፍሎች ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ በኢንስቲትዩቱ ግቢ ውስጥ በመምጣትና የሚከራዩ ቦታዎችን በማየት በግልጽ ጨረታ መሳተፍና መከራየት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሰነዶች አሟልተው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሰርተፊኬት ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ክፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችል
- በውድድሩ የሚሳተፉ ተጫራቾች በዘረፉ ፈቃድ ያላቸው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማረጋገጫ ሰርተፊኬትና በጨረታ ለመሳተፍ ከአገር ውስጥ ገቢ ቢሮ ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 111 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ አስራ ቀናት ውስጥ ኢንስቲትዩቱ ድረስ በመቅርብ የጨረታ ሰነዱን 500 (አምስት መቶ ብር ) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር ብር 111 የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 4:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው :: ጨረታው የሚከፈተው በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 የሚከፈት ይሆናል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ክፍል ብር 50,000.00 ብቻ ሲፒኦ : በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ወይንም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመቤታችን ጋር ውል ሲይዙ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ውል የሚይዘው ለአንድ አመት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ዋጋ ሲሞሉ ለአንድ ካሬ ለአንድ ወር ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ይከፈታል
- በዚህ ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል ።
- መ/ቤቱ ስለ ኪራዩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተሉትን አድራሻዎች መጠቀም ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት መገናኛ ከአምቼ ጎን /ቃል ህንጻ ፊት ለፊት/ የስልክ ቁጥር 011 6670973
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት
