በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ ለ2017 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር/ግ/ጨ 003/2017 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ ለ2017 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ፡-
ሎት 1፡-የደንብ ልብስ ግብዓቶች፣
ሎት 2፡- አላቂ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣
ሎት 3፡- የኅትመት ሥራዎች፣
ሎት 4፡- መድኃኒት ሪኤጀንቶች እና ቋሚና አላቂ የሕክምና መገልገያ ዕቃዎች፣
ሎት 5፡ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣
ሎት 6፡- ሌሎች አላቂ ዕቃዎችና መሣሪያዎች፣
ሎት 7፡ ፈርኒቸር፣
ሎት 8፡ ኤሌክትሮኒክስ፣
ሎት 9፡ ለጥገና የሚያገለግሉ ዕቃዎች፣
ሎት 10፡ ልዩ ልዩ የጥገና ዕቃዎች ሥራዎች የውሃ መስመር ጥገና እና የትራንስፖርት አገልግሎት / በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሣተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ፤
- በኣቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ያቀረቡት ማስረጃ በዌብሣይት የሚረጋገጥ፤
- እንደአስፈላጊነቱ ለአገልግሎት ሥራዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 በሚገኘው የግዢ ክፍል ቀርበው የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ናሙና በዕቃው ዓይነት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት ዋና እና ኮፒ ሠነዶችን እንዲሁም ለናሙና የሚቀርቡ የዕቃውን ስም የሚገልፁ የዕቃዎች ናሙና የፎቶግራፎች ናሙና ለየብቻ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለተጫራቾች ጨረታው እንደተጠናቀቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን
|
የሎት ቁጥር |
የሎት መግለጫ |
የሚያሲይዙት የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ ልክ |
|
ሎት1 |
የደንብ ልብስ ግብአቶች |
2,000.00 |
|
ሎት2 |
አላቂ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች |
3,000.00 |
|
ሎት3 |
የህትመት ስራዎች |
1,000.00 |
|
ሎት4 |
መድሃኒት ሪኤጀንቶች እና ቋሚና አላቂ የህከምና መገልገያ ዕቃዎች |
75,000.00 |
|
ሎት5 |
አላቂ የፅዳት ዕቃዎች |
5,000.00 |
|
ሎት6 |
ሌሎች አላቂ ዕቃዎችና መሣሪያዎች |
1,000.00 |
|
ሎት7 |
ፈርነቸር |
2,000.00 |
|
ሎት8 |
ኤሌክትሮኒክስ |
5,000.00 |
|
ሎት9 |
ለጥገና የሚያገለግሉ ዕቃዎች |
1,000.00 |
|
ሎት10 |
ልዩ ልዩ የጥገና ዕቃዎች ሥራዎች የውሃ መስመር ጥገና እና የትራንስፖርት አገልግሎት |
1,000.00 |
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት ወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ወይም በዘርፉ ከተደራጁበት ወረዳ ጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ቤት የተፃፈ ሕጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ አስራ አንደኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ2፡30 ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታ ሠነድ መቀበያ ጊዜ የበቃ መሆኑን የሚገልጽ ቃለ ጉባኤ በመያዝ ተዘግቶ በዚያው ዕለት እና ሰዓት ከ30 ደቂቃ ከጠዋቱ 3፡00 የመክፈቻ ቃለ ጉባኤ ተይዞ ሲታሸግ የነበሩ ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
በዚህ ዕለት
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲገኙ ይጋበዛሉ፤ ባይገኙ ግን የጨረታ መዝጊያውንም ሆነ መከፈቻ
- ቀኑን ወይም ሰዓቱን ማራዘም አይቻልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ብቻ ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር: 0112-29-12-50 ወይም በኢሜይል አድራሻችን፡- akw3hc@gmail.com ወይም ሊያገኙን ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡- በአውቶብሰ ተራ ወደ ሰባተኛ ወይም ከሰባተኛው ወደ አውቶብስ ተራ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ሲሄዱ ከዋይ ዜድ ህንፃ ወደ መካነሠላም ሆቴል በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ያህል እንዲሄዱ ባለ አራት ፎቅ ህንፃ ላይ/በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ በሚል ስያሜ ያገኙናል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ
