በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ ለ2017 በጀት አመት ለአገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2017
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ ለ2017 በጀት አመት
- ልዩ ልዩ የጽዳት እቃዎች፣
- የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- የደንብ ልብስ ጨርቅ፣ ጫማ፣
- የህትመት ውጤቶች፣
- መድሀኒቶች እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች፣
- ቋሚ የህክምና መሳሪያዎች ሌሎች
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የጥገና እና
- ፓርቲሽን ስራ አገልግሎት፤ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡-
- የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የዘመኑ ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ፣ የመድሀኒት አቅራቢ የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት፣ ለጥገናና ፓርቲሽን ስራ ቢያንስ ደረጃ 6 የብቃት ማረጋገጫ የሚያቀርቡ እና በአቅራቢ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት (በስራ ሰዓት) በጤና ጣቢያው 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በሚገኘው ግዥ ከፍል በመቅረብ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለየምድቡ(ሎት) የተመደበውን የብር መጠን በCPO ማስያዝ አለባቸው፡፡ ከአንድ በላይ በሆነ ሎት የሚሳተፉ ተጫራቾች ለየሎቱ የተመደበውን የብር መጠን ድምር በ CPO ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነዶች እና የሞሉትን ዋጋ ዋና እና ኮፒ በፖስታ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ በወጣ እስከ ከ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጤና ጣቢያው 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ዋጋ ማቅረብ ያለባቸው ከጤና ጣቢያው በሚወስዱት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብቻ ነው::
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- የህትመት ውጤቶች ጤና ጣቢያው በሚያቀርበው ናሙና መሰረት የሚዘጋጁ ይሆናል፡፡
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- አራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ስሙ ሰሜን መዘጋጃ
ስልክ ቁጥር :- 0118-12-68-04/12-29-60
ሰሜን ጤና ጣቢያ
