በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የሁልበረሰግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የሁልበራግ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ለሆነው ሎዳር ማሸን የሚሆን ጎማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የሁልበራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የሁልበረሰግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የሁልበራግ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ለሆነው ሎዳር ማሸን የሚሆን ጎማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ:-
- በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ፤
- በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ እውቅና ባለው ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ በ15 ቀናት ውስጥ በማ/ኢ/ክ/መ/በስልጤ ዞን ሁ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በአካል/በተወካይ አማካኝነት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላል፡፡ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በስም በታሸገው ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሁ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ለዚህ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው ከወጣ ከ15ኛው ቀን በኋላ ባለው የስራ ቀን 8:30 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 9:00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
-
- ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
- የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጠውም።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0911660491/0921001167 ይደውሉ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የሁልበራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
