በልደታ ከ/ከተማ የጄነራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ መድሐኒት እና የህክምና እቃዎች የጥገና እቃዎች የፅዳት እቃ፣ የደንብ ልብስ ስፌት እና ቋሚ የፅህፈት እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በልደታ ክ/ከተማ የጄነራስ ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ
የሶስተኛ ዙር የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ከ/ከተማ የጄነራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ መድሐኒት እና የህክምና እቃዎች የጥገና እቃዎች የፅዳት እቃ፣ የደንብ ልብስ ስፌት እና ቋሚ የፅህፈት እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ፡-
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑ ግብር ለመከፈላቸው የታደል ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
- በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በጤና ጣቢያው እረዳት ፋይናንስ ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 መድሐኒትና ህክምና እቃ ብር 10,000፣ ሎት 2 የጥገና እቃ ብር 3000፣ ሎት 5 ደንብ ልብስ ብር 3000፣ ሎት 6 የፅዳት እቃ ብር 4000 ሎት 7 የቋሚ እቃ ብር 6,000 በCPO/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የእቃ አይነት (ሳምፕል) ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡትን እቃ ዋጋ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት የግዥውን አይነት በኤንቬሎፑ ላይ በመጥቀስና ማኅተም በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጤና ጣቢያዉ ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን እለቱ በአል ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን ተጫራች አባላት በተገኙበት በጤና ጣቢያው አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ አሟልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም፡፡
- ጤና ጣቢያው የሚጫረተውን እቃ ብዛት አስፈላጊነቱ በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ የሚችል ሲሆን ተጫራቾች ላሸነፉት እቃ የአንድ ዓመት ዋስትና መስጠት አለባቸው፡፡
- ጤና ጣቢያው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ፡- ብስራተ ገብርኤል አደባባይ የኢ/መ/ፋ/ፊት ለፊት ልደታ ከ/ከተማ የጄነራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር :- 0118347500 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በልደታ ክ/ከተማ የጄነራስ ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ
