በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በጋሳውዴ ቀበሌ በጂፓ መንደር ያለውን በቁጥር 3891 የፈረንጅ ጽድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልፅ የጨረታ ቁጥር ፡- 007/2017
በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በጋሳውዴ ቀበሌ በጂፓ መንደር ያለውን በቁጥር 3891 የፈረንጅ ጽድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር በመክፈል ፈቃድ ያሳደሳችሁ እና ከግብር ነጻ መሆናችሁን የሚገልጽ ደብዳቤ፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በCPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ በእኖር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከእኖር መረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው::
- ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስሪያ ቤቱ የጨረታው ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 /ስልሳ/ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 09-28-01-17-46 ወይም 09-10-10-67-16 ይደውሉ፡፡
በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
