ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ልዩ ልዩ የህትመት ወረቀቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ልዩ ልዩ የህትመት ወረቀቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር ፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት እና የንግድ ሰርተፍኬት እና ሌሎች የህጋዊነት ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ቢሮ ቁጥር 10 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከግዥ ቡድን በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ባለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ታሽጐ በ8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ይሁን እንጂ የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ስልክ ቁጥር ... 011 551 24 66/ 011 515 50 05
ፋክስ 011 551 86 96
ፖ.ሣ. ቁጥር 2365
ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
አዲስ አበባ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የ/የግ/ማህበር
