Tender Detail

Tender Details

  • Company በቂርቆስ ክ/ከተማ የጤና ጽ/ቤት እፎይታ ጤና ጣቢያ
  • Address ቦሌ ማተሚያ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ከዳንዲቦሩ ትምህርት ቤት ጀርባ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118963471
  • Website
  • Deadline05 Feb 2025, 5:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በቂርቆስ ክ/ከተማ የጤና ጽ/ቤት እፎይታ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በቂርቆስ ክ/ከተማ የጤና ጽ/ቤት እፎይታ ጤና ጣቢያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በቂርቆስ ክ/ከተማ የጤና ጽ/ቤት እፎይታ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ፡-

1. የደንብ ልብስ 2. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች 3. ለፕላንት ለማሸነሪና ለማሽነሪና እድሳትና ጥገና 4 ለፕላንት ለማሽነሪና ለመሳሪያ መግዣ (ቋሚ ዕቃዎች)  5 አላቂ የህክምና ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡30 በጤና ጣቢያው አራተኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 400 መግዛት ትችላላችሁ፡፡

 

 ተ.ቁ

 የዕቃው ዝርዝር በሎት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ

 ሎት 1. 6211

 ለደንብ ልብስ

 3000

 ሎት2. 6219

 ልዩልዩ መሳሪያዎች

 3000

 ሎት3. 6243

 ለፕላንት ለማሽነሪና ለማሽነሪና እድሳትና ጥገና

 3000

 ሎት4. 6313

 ለፕላንት ለማሽነሪና ለመሳሪያ መግዣ

 5000

 ሎት5. 6214

 አላቂ የህክምና ዕቃዎች

 5000

 

  1. ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል ባላቸው እቃዎች ላይ ናሙና ከጨረታው መክፈቻ እለት ከሁለት ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች በኤንቨሎፕ በማሸግ በሁለት ፖስታ በማድረግ እላያቸው ላይ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ያቀረቡትን CPO ኦሪጅናል ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል። የጨረታው መዝጊያ እለት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  3. ጨረታው ጋዜጣ ላይ በወጣበት በ10ኛው ቀን 11፡30 (አስራ አንድ ተኩል) ታሽጎ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዓል ከሆነ ወይም የረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእፎይታ ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  4. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን አረጋግጦ ውል ከተዋዋለ በኋላ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ በ7 ቀን (ሰባት ቀን ውስጥ) የማቅረብ ኃላፊነት አለበት፡፡
  5. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው:: መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በቂ/ክ/ከተማ ጤ/ጽ/ቤት እፎይታ ጤና ጣቢያ ልዩ ቦታው ቦሌ ማተሚያ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ከዳንዲቦሩ ትምህርት ቤት ጀርባ ይገኛል፡፡

 

መረጃ ለመጠየቅ 0118963471/68

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስ/የቂርቆስ ክ/ከተማ እፎይታ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender