የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ አቅርቦቶችን ለማሟላት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Amhara Region Police College (የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ)
አገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ብግጨ 001/2017
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ አቅርቦቶችን ለማሟላት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፤
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- የተሽከርካሪ ጎማ
- የጽህፈት መሳሪያዎች
- የጽዳት እቃዎች
- ሌሎች የቢሮ መገልገያ ቋሚ እቃዎች
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች፤
- የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይነት ማስረጃ /TIN/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ሰነድ ደብረማርቆስ ከተማ በአዲሱ ግቢ አማራ ከልል ፖሊስ ኮሌጅ ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብር በመክፈል እስከ 15ኛው ቀን ድረስ መግዛት አለባቸው።
- ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ከዋለ ዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ሆኖም 16ኛው ·ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጧቱ በ3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ስፍራ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የተወዳዳሪዎች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግድም።
- የእቃዎችን ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
- ኮሌጁ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0587714207/0587714199
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ
