ወላይታ ዞን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በኮካቴ ማራጫሬ ችግኝ ጣቢያ ውስጥ ለበረካታ ዓመታት (ዕድሜ ጠገብ) እንጨቶች ማለትም ፓይነስ ፓቹላ ፤ ባህርዛፍ የፈረንጅ ጽድ እና ግራቨሊያ እንጨቶችን ለተለያዩ ዓለማ ላይ የሚውል ደን ዛፎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡
ወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት
ለበርካታ ዓመታት (ዕድሜ ጠገብ ) እንጨቶች
ሽያጭ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ወላይታ ዞን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በኮካቴ ማራጫሬ ችግኝ ጣቢያ ውስጥ ለበረካታ ዓመታት (ዕድሜ ጠገብ) እንጨቶች ማለትም ፓይነስ ፓቹላ ፤ ባህርዛፍ የፈረንጅ ጽድ እና ግራቨሊያ እንጨቶችን ለተለያዩ ዓለማ ላይ የሚውል ደን ዛፎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ፡-
1/ ማንነቱን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ እና የጨረታ ሰነድ በገዙበት ደረሰኝ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
2/ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከላይ የተገለጹ ፓይነስ ፓቹላ፤ ባህርዛፍ የፈረንጅ ጽድ እና ግራቭሊያ በዝርዝር የያዘውን የመወዳደሪያ ሰነድ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
3/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለጨረታ ከሚያስገባው ገንዘብ መጠን ጠቅላላ 4% (አራት በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4/ የጨረታ ሣጥን ጋዜጣው ከወጣበት 15 ተከታታይ ሥራ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከሰዓት 8፡45 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል፡፡
5/ የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ ያሸነፈበትን ዋጋ በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የባንክ አካውንት ሙሉ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ያሸነፈውን ደን እንጨቶችን ወዲያውኑ ይረከባል። ሌሎች ዝርዝር ሂደቶች በጨረታ ሰነዱ የሚካተቱ ይሆናል።
6/ አሸናፊ በሆኑበት ደን እንጨቶች ሽያጭ በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ስምምነት ውል ለመግባት ፍቃደኛ ካልሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
7/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ገዝተው የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ሶዶ ዙ/ወ/አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመሆን በኮካቴ ማራጫሬ ችግኝ ጣቢያ ውስጥ ያለውን የፓይነስ ፓቹላ ፤ ባህርዛፍ የፈረንጅ ጽድ እና ግራቨሊያ እንጨቶችን ሄደው ማየት ይችላሉ፡፡
8/ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046-180-6026 ደውለው
ማነጋገር ይችላሉ፡፡
ወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት
