በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በምስ/ጎጃም ዞን ጎንቻሲሶ እነሴ ወረዳ 01 ቀበሌ ምጣድ ዱር የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን 620.11 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ቁም ደን፣ በደ/ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ሁለቱ ወገዳሜ ቀበሌ ገልዳማይ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን 3048.50 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ፣ 957.39 ሜ/ኩብ የነጭ ባህር ዛፍ ቁም ደን በድምሩ 4005.89 ሜ/ኩብ ፣ በደ/ታቦር እንጨት መሰንጠቂያ የተመረተ 87.14 ሜ/ኩብ ጣውላ እና በአዊ ዞን ባንጃ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኘውን 23,091.41 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)
የቁም ደንና የጣውላ ምርት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በምስ/ጎጃም ዞን ጎንቻሲሶ እነሴ ወረዳ 01 ቀበሌ ምጣድ ዱር የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን 620.11 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ቁም ደን፣ በደ/ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ሁለቱ ወገዳሜ ቀበሌ ገልዳማይ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን 3048.50 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ፣ 957.39 ሜ/ኩብ የነጭ ባህር ዛፍ ቁም ደን በድምሩ 4005.89 ሜ/ኩብ ፣ በደ/ታቦር እንጨት መሰንጠቂያ የተመረተ 87.14 ሜ/ኩብ ጣውላ እና በአዊ ዞን ባንጃ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኘውን 23,091.41 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራች ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የሽያጩ መጠን 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተእታ /VAT/ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡትን ቁም ደን ምርቶች ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተ ማየት ይችላሉ ።
- የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 24 እና በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ (ደ/ብርሃን፣ ደ/ታቦር ፣ደ/ማርቆስ፣ እንጅባራና ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤቶች) የማይመለስ 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን በኦሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋን ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያ ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06፣ ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች "የቁም ደንና የጣውላ ምርት የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ" ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን በ 4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፤
- ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም፡፡ ሆኖም አሸናፊው በአሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል፡፡
- ተጫራቾች ቁም ደኑን በተመለከተ ቅልቅል ደን ተብሎ የቀረበውን ክፍልፋይ ሁሉንም አይነት ምርት ክፍልፋይ ሎት /ምድብ/ በመሙላት ማንሳት ይጠበቅባቸዋል የጣውላ ምርቱን ሁሉንም ማንሳት ይጠበቅባቸዋል። ደንበኛው ከአሁን በፊት ምርት ገዝቶ ክፍያ ያላጠቃለለ ከሆነ ክፍያ እስከሚጨርስ ድረስ ሌላ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችልም።
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ባ/ዳር 0582263095፣ ታቦር 0584410306፣ ደ/ብርሃን 01163750117፣ እንጅባራ 582270485፣ደ/ማርቆስ 0588719004፣ ኮ/ቻ 0914716636 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ
ባሕር ዳር
