የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሱሉልታ ካምፓስ የሚገኙ የተለያየ መጠን ያላቸው የባህር ዛፎችን እና ግራቪያን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አአልአ/ግጨ /01/2017
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሱሉልታ ካምፓስ የሚገኙ የተለያየ መጠን ያላቸው የባህር ዛፎችን እና ግራቪያን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች :-
- የታደሰ አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የቲን (TIN) የምዝገባ ወረቀት የሚያቀርቡ፡፡
- ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት በጨረታ ለመካፈል ለመሳተፍ የሚያስችል የወቅቱ ግብር ገቢ ስለመሆኑ ማስረጃ ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በአካዳሚው ገንዘብ ቤት በመክፈል መወሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸውን ከተፈላጊ መረጃዎች ጋር በፖስታ በማሸግ በአካዳሚው የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአካዳሚው የግዥ ቡድን ቢሮ በግልጽ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መከፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ሰነድ CPO በአካዳሚው ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተመረጡ የውል ማስከበሪያ ውሉ ከመፈረሙ በፊት የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ዛፎቹን ቆርጦ ከአካዳሚው ግቢ ማንሳት አለባቸው፤
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0116 67 49 10 ደውሉ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
አድራሻ ፡- ቦሌ ጃፓን አጠገብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ጃፓን ቅርንጫፍ የሚገኝበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ
