Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ/ክ/ከተማ የወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ
  • Address በአዲሱ የካራ መንገድ ከአቅም ግንባታ ጀርባ እና ወሰን ግሮሰሪ 200 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 8 93 25 88
  • Website
  • Deadline29 Jan 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ/ከ/ከተማ የወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ የተለያዩ አላቂ የህክምና እቃዎች መድሃኒቶች የደንብ ልብስ ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች እና የተለያዩ ህትመቶች እና የህንፃና ጥገና ስራዎች አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት/ ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ/ክ/ከተማ የወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ


 

የጨረታ  ማስታወቂያ

  የጨረታ  ቁጥር 002/2017

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ/ከ/ከተማ የወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ የተለያዩ አላቂ የህክምና እቃዎች መድሃኒቶች የደንብ ልብስ ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች እና የተለያዩ ህትመቶች እና የህንፃና ጥገና ስራዎች አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት/ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው:
  2. ንግድ ፍቃድ ያደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢና አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡
  4. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 4ተኛ ፎቅ ቢቁ 408 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሂሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው ።
  6. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ፣ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ኮፒ በአራት ፖስታ የሚወዳደሩበትን አይነት በፖስታው ላይ በመለየት - ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ/ ወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 408 በመገኘት ለዚህ የተዘጋጀው የተጫራቾች ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ። ቴክኒካል ኦርጂናል (ህጋዊ ሰነዶች) ኮፒ ተደርገው የድርጅቱ ማህተም የተደረገበት
  7. ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሎሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 408 በኮሚቴዎች ይከፈታል።
  8. እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት እና ሙሉ ሰነዱን ሳይገነጠል መመለስ አለበት ይህን ያልተገበረ ተጫራች ውድቅ ይደረጋል ።
  9. መ/ቤታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ በመስሪያ ቤቱ ስም ለሎት1 4000 ብር አራት ሺህ ብር / ለሎት2፣ 24000 ብር /ሃያ አራት ሺህ ብር/ ለሎት3 ፤ 12400 ብር /አስራ ሁለት ሺህ አራት መቶ ብር/ ለሎት4 ፣ 3500 ብር /ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለሎት5 ፣3000 ብር /ሶስት ሺህ ብር/ ለሎት6 ፣ 3400 ብር /ሶስት ሺህ አራት መቶ ብር/ ለሎት7 ፣ 3000 ብር /ሶስት ሺህ ብር/ ለጥቃቅን ህጋዊ ደብዳቤ ከዚህ ውጪ የሚመጡ የጨረታ ማስከበሪያ አንቀበልም፡፡
  11. ተጫራቾች በሰነዱ ላይ የተካተተውን መረጃ በሙሉ ሞልተው መላክ ይኖርባቸዋል።
  12. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉት ስራ 10% ለአሸነፉት ስራ የውል ማስከበሪያ የሚያስይዙ መሆኑን ማወቅ አላበቸው።
  13. ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ሳያሟላ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከርና ጨረታውን ለማሳሳትና ለማጭበርበር የሚሞክር ተጫራች ከጨረታ ይሰረዛል።
  14. ተጫራቾች ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

 

አድራሻ ፡- የለሚ ኩራ/ክ/ከተማ/ወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ

ስልክ ቁጥር :- 011 8 93 25 88/011 8 93 22 55/011 8 93 29 88

በአዲሱ የካራ መንገድ ከአቅም ግንባታ ጀርባ እና ወሰን ግሮሰሪ 200 ሜትር ገባ ብሎ

 

በአዲስ  አበባ  ከተማ  አስተዳደር  በለሚ  ኩራ/ክ/ከተማ

የወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender