የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዘመናዊ እና ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ የመኪና ማቆሚያ ሥርዓት፣ የጥገና፣ የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት አስተዳደር በገቢ መጋራት አሠራር (Concession Business Modality) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር :- SSNT-T518
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዘመናዊ እና ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ የመኪና ማቆሚያ ሥርዓት፣ የጥገና፣ የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት አስተዳደር በገቢ መጋራት አሠራር (Concession Business Modality) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
-
- በመኪና ማቆያ (ፓርኪንግ) አገልግሎት ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው : የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ቢያንስ አምስት (5) ዓመት በአገልግሎቱ የሥራ ልምድ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ትውልደ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ የኢትዮጵያ መታወቂያ/ቢጫ ካርድ ያለው፣ ሕጋዊ እና በመኪና ማቆሚያ አገልግሎት የሥራ ፈቃድ ያለው እና በሚሠሩበት አገር ቢያንስ አምስት (5) ዓመት የሥራ ልምድ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT -T518 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢ-ሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢ-ሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ብር 300.000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከኢንሹራንስ እና ቅደመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ቅጂውን ቴክኒካል ሰነድ፣ ዋናውን እና ቅጂውን ፋይናንሻል ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
በስልክ ቁጥር: +251-115-17-89-18 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
ኢሜል፡ ESAYASTS@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ።
