Tender Detail

Tender Details

  • Deadline21 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle tire

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሽከርካሪ ጎማ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡


 

የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  EEP/ST/NCB/15/2017

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሽከርካሪ ጎማ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ የጨረታ ሰነድ እንዲሸጥላቸው የጨረታ መለያ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለጽ ፣ በሚመለከተው ኃላፊ የተፈረመ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ወጪ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፡፡
  4. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሕንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-- 9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የተሽከርካሪ ጎማ ግዥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/15/2017 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት  ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

 

 ተ.ቁ

 Description

 የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ

 የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት

 የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት

 1

 የተሽከርካሪ ጎማ ግዥ

 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)

 ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

 ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

 

  1. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ።
  2. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ሁሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ  ኃይል

Save Tender