Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
  • Address Lagar, Ras Mekonen Ave, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011-551 24 00
  • Websitehttps://eic-et.com/branches/
  • Deadline31 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Printing And Publishing

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለ2018 ዓ.ም የሥራ ዘመን የሚያገለግሉ አጀንዳዎችንና ቀን መቁጠሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፡- ኢአድ/ግንአዳ/006/2017

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለ2018 ዓ.ም የሥራ ዘመን የሚያገለግሉ አጀንዳዎችንና ቀን መቁጠሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 

ምድብ

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

ብዛት

ምድብ 1

1.

 መካከለኛ አጀንዳዎች (Diary)

 40,000

2.

 ልዩ አጀንዳዎች (Diary)

 5,000

ምድብ 2

1.

 የግድግዳ ቀን መቁጠሪያዎች

 3,000

2.

 የጠረጴዛ ቀን መቁጠሪያ

 30,000

 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረ-ገጹ (website) አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ታክስ ከሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከው ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለምድብ አንድ ብር 400,000.00 (ብር አራት መቶ ሺህ
    )
    እንዲሁም ለምድብ ሁለት ብር (155,000.00 (ብር አንድ መቶ ሃምሳ አምስት ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዝ (CPO) ወይም ለዘጠና (90) ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንተርፕራይዝ አገልግሎት ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ በሚከተለው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከፈታል። ምድብ 1 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት እንዲሁም ምድብ ሁለት ከቀኑ 8፡45 ሰዓት ይከፈታል።
  6. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011-5-51-24-00 የውስጥ መስመር 237/262 ወይም በቀጥታ 011-5-50-49-31 መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

 

Save Tender