በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተደዳር ትምህርት ጽ/ቤት ለትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ መጽሀፍቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሳተም ይፈልጋል።
የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተደዳር ትምህርት ጽ/ቤት ለትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ መጽሀፍቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሳተም ይፈልጋል፤ ስለሆነም፣-
* በመስኩ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
* የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
* የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
* በመንግስት ግዢ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
* የጨረታ ዋስትና 40,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፤
ተጫራቾች ሰነዱን ከወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ እለት በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ ፡-
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- 046-7-71-02-11 ይደውሉ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተደዳር ትምህርት ጽ/ቤት
