የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት የ2017ዓ.ም በጀት አመት የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ወረዳ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት የ2017ዓ.ም በጀት አመት የሚያስፈልጉ
ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣
ሎት 2 የተለያዩ ህትመቶች፣
ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣
ሎት 4 ቋሚ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው፣
- የአገልግሎት መጠን ከብር 200.000 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር መወዳደር ለሚፈልጉት እያንዳንዱ ሎት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /አምሳ ብር/ በመክፈል ከግዥ ክፍያና ንብረት አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 22 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 28 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን እስከ 4፡00 የጨረታ ሰነድዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው 30/04/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው ከሎት 1 ሎት3 በሎት ጠቅላላ ድምር ሲሆን ሎት4 በነጠላ ዋጋ ይሆናል፡፡
- የእቃውን ማንኛውንም ማጓጓዣ ወጪ ችሎ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ።
- የጨረታ አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 28 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0335511147 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ወረዳ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት
