የምስራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ውስጥ ለሚገኙት የህግ ታራሚዎች ለምግብ አቅርቦት የሚውል ጥሬ እህል ለ 2017 ዓ.ም በጀት ለሁለተኛ ዙር ከጥር 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ለ 6 (ስድስት) ወር በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ውስጥ ለሚገኙት የህግ ታራሚዎች ለምግብ አቅርቦት የሚውል ጥሬ እህል ለ 2017 ዓ.ም በጀት ለሁለተኛ ዙር ከጥር 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ለ 6 (ስድስት) ወር በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ማንኛውም በጨረታ ውል መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ፤
- የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ወይም ቢሮ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና አግባብነት ያለው 2016 የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር (TIN) የተመዘገቡ ወይም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው ።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 (ሰላሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞኑ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞን ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከመቶ ሁለት ፐርሰንት (2%) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) እና የምግብ እህል ናሙና ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
- በጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ ተደራጅቶ የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማኅበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ፡፡ ይህ ካልተገኘ በጥሬ እህል እናወዳድራለን ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በስራ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት በዞኑ ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የህግ ታራሚ ኮሚቴዎች እና የማረሚያ ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከፈታል።
- የዞኑ ማረሚያ ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተዘጋጀ ማብሰያ ቤት ውስጥ ምግብ አብስሎ መቅረብ የሚችል፤
ማረሚያ ቤቱ የሚገኝበት ከተማ
|
ተ.ቁ |
የዞን ማረሚያ ቤት |
የሚገኝበት ከተማ |
|
1 |
የምስራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት |
ጊንር |
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡ 0911645276/ 0911803891 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የምስራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት
