የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሁሉም በረራዎቹ ላይ የሚያቀርበውን የሰላምታ መጽሔት ማተም የሚችሉ መጽሔት የማተም ልምድ ያላቸውን የሀገር ውስጥ የህትመት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ከ3-5 አመት በኮንትራት ማሠራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: - SSNT-T512
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሁሉም በረራዎቹ ላይ የሚያቀርበውን የሰላምታ መጽሔት ማተም የሚችሉ መጽሔት የማተም ልምድ ያላቸውን የሀገር ውስጥ የህትመት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ከ3-5 አመት በኮንትራት ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ሁሉም የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ሰነዶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በህትመት አገልግሎት 3 ዓመት እና ከዛ በላይ የሰሩ ፣ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ናሙና የህትመት ውጤቶችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር ሰላሳ ሺህ /30,000.00 ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ (CPO) ወይም ለ90 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ለመውሰድ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ጨረታ ቁጥር (SSNT- T512) በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢሜል ያገኛሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካል፣ ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፌያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-8025
ኢ-ሜይል: HELENN@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
