በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደዉሃ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቡድን በስሩ ለሚያስተዳድረው ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በCIP በጀት ሎት 1 እስቴሽነሪ እቃዎች ANRS G/WUHA - CIP G-01/24/25 ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደዉሃ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደዉሃ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቡድን በስሩ ለሚያስተዳድረው ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በCIP በጀት:-
ሎት 1 እስቴሽነሪ እቃዎች ANRS G/WUHA - CIP G-01/24/25 ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 (እስቴሽነሪ) 2000 (ሁለት ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው። በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ተጫራቾች በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታው ላይ የሚወዳደሩበትን የግዥው አይነትና ሎት በመፃፍ በገንዳ ውሃ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ለጨረታ ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከገ/ውኃ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ በብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ። ስለሆነም ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገ/ውኃ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በግልፅ ይከፈታል፡፡
- የአብከመ ግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1/2003 እና በተጨማሪ በቢሮው የወጡ የመመሪያ ማሻሻያዎች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደዉሃ ከተማ አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት
