የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያየ አይነት ቶነሮችን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ (በማዕቀፍ ስምምነት) አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/14/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያየ አይነት ቶነሮችን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩና ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ (በማዕቀፍ ስምምነት) አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ የጨረታ ሰነድ እንዲሸጥላቸው የጨረታ መለያ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለጽ፣ በሚመለከተው ኃላፊ የተፈረመ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ወጪ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተለያየ አይነት ቶነሮች ግዥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/14/2017 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
|
ተ.ቁ |
Description |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
የተለያየ አይነት ቶነሮች ግዥ |
ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) |
ታኅሣሥ 23 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ታኅሣሥ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ዓ.ም |
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ፡፡
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
