Tender Detail

Tender Details

  • Company ላላምባ አሶሴሽን መንግስታዊ ያልሆነ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09 21 22 15 92
  • Website
  • Deadline24 Dec 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

በደ/ም/ኢት/ሕ/ክ/መ/ካፋ ዞን አውራዳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኘው ላላምባ አሶሴሽን መንግስታዊ ያልሆነ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር የ2024 ዓ.ም የሒሳብ መዝገቦችን በሙሉ በገለልተኛ አዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

ላላምባ አሶሴሽን መንግስታዊ ያልሆነ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት


የኦዲት  ጨረታ  ማስታወቂያ

 

በደ/ም/ኢት/ሕ/ክ/መ/ካፋ ዞን አውራዳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኘው ላላምባ አሶሴሽን መንግስታዊ ያልሆነ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር የ2024 ዓ.ም የሒሳብ መዝገቦችን በሙሉ በገለልተኛ አዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ደርጅቱ ከታች የተዘረዘሩ ስራዎችን ለማስመርመር ይፈልጋል::

  • የድርጅቱ የ2024 ዓ.ም የሒሳብ መዝገቦችን በሙሉ ያስመረምራል
  • የሒሳብ ሰነዶቹ በቁጥር 3 ቦክስ ፋይል ይሆናሉ
  • የኦዲት ድርጅቱ ስራውን ሲያጠናቅቅ የኦዲት ሪፖርቱን እና ማኔጅመንት ሪፖርት ዋና ሰነድ በአምስት ቅጅ ለድርጅቱ ያስረክባል
  • የሲቪል ማኅረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በሚጠይቀው የኦዲት መስፈርት መሰረት ያከናውናል ከስራው አስቸኳይነት የተነሳ የኦዲት ድርጅቱ ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማለትም ቢበዛ ውል በተፈረመ አስራ አምስት ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅና ሪፖርቱን ማስገባት ይኖርበታል፡፡

የኦዲት  ድርጅቱ  ማሟላት  የሚጠበቅበት  ሁኔታዎች

  • የታደሰ የንግድ ፈቃድ
  • የዘመኑ ግብር ስለመከፈሉ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
  • ቢያንስ በሙያው 4 ዓመትና ከዚያ በላይ የሰራ
  • የሲቪል ማኅረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበ
  • በአካውንቲንግና በኦዲት ቦርድ ፈቃድ ያለው

ስለዚህም ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ስራዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት የተጠቀሰውን መስፈርት በሙሉ የምታሟሉ ማንኛውም የኦዲት ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ከሚከተለው አድራሻችን በመጠቀም እንዲመዘገቡ እናሳውቃለን ።

አድራሻ ፡- ላላምባ አሶሴሽን

1. ፖስታ ሳጥን ቁጥር 102

2. በአካል በመቅረብ ለቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ማመልከት ለሚፈልጉ ደ/ም/ኢት/ሕ/ክ/መ/ ካፋ ዞን አውራዳ ከተማ አስተዳደር ::

ስልክ  ቁጥር ፡- 09 21 22 15 92

 

ላላምባ  ማኅበር

Save Tender