የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር (EAGC-ADA) በማህበሩ AABE ስር የተመዘገቡና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ብቁ የተረጋገጠ የኦዲት ኩባንያዎች አወዳድሮ እ.ኤ.አ January 01, 2024 እስከ December 31/2024 ያሉትን የልማት ማህበሩን ሂሳብ በ IPSAS ኦዲት ማስደረግ ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታ ልማት ማህበር (EAGC-ADA)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር (EAGC-ADA) በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሲቪል ማኅበራት ባለስልጣን የተመዘገበ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው። በመሆኑም ልማት ማህበሩ AABE ስር የተመዘገቡና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ብቁ የተረጋገጠ የኦዲት ኩባንያዎች አወዳድሮ እ.ኤ.አ January 01, 2024 እስከ December 31/2024 ያሉትን የልማት ማህበሩን ሂሳብ በ IPSAS ኦዲት ማስደረግ ያስፈልጋል። ድርጅቱ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ሲኖሩት ለእያንዳንዱ ፕሮጀከቶች ማለትም 24 የተናጥል እና አጠቃላይ 1 (Consolidated) የድርጅቱ ኦዲት ሪፖርት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ተጋባዥ ተጫራች ድርጅቶች
- የሙያ ማረጋገጫ
- የኢትዮጵያ አካውንቲንግ እና ኦዲቲንግ ቦርድ (AABE) ጽ/ቤት የምስክር ወረቀት ኮፒ
- የቲን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ኮፒ
- የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ኮፒ
- የሰራተኞች ስብጥር እና ጠንካራ መገለጫ፤ ዋና አጋርን ጨምሮ
- የ NGO ጋር ቀደም ያለ የኦዲት ተሞክሮ እና በ IPSAS ላይ የተመሰረተ የሂሳብ አያያዝ መረጃ ማቅረብ የሚችል
- የጊዜ ገደብን፤ የመጨረሻ የኦዲት ሪፖርት ማቅረቢያ ቀን የሚያሳውቅ
- ለአዲት ስራው ሌላ አግባብነት ያለው መረጃ የሚያቀርብ፣ የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ዋጋ የታሸጉ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ አስር የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰአት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
የበጀት ዓመቱ የየሒሳብ መዛግብት በአ.አ ከማህበሩ ጽ/ቤት በመገኘት መመልከት ይችላሉ። ማህበሩ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር በኢትዮ ቻይና መንገድ ወንጌላዊት ህንጻ አጠገብ ሜሪስቶብስ ክሊኒክ ከፍ ብሎ በሚገኘው ቢሯችን ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 251-916-79-04-12
የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታ ልማት ማህበር (EAGC-ADA)
